ትላንት
YesterdaY
የዓለም ሕዝብ ለአሥር ሺህ ዓመታት ወደ ኋላ ተጉዞ የሚያገኘው ታሪክ የአዳኝና የፍራፍሬ ለቃሚ ማህበረሰብ ደረጃን ነው። ይህንን የማህበረሰብ ዕድገት ለታዳጊ ልጆቻቸው ታሪክ አድርገው ይተርኩታል። እኛ ኢትዮጵያዊያንስ? ዓለም ወደ ኋላ ጥሎት ያለፈውን ሕይወት ዛሬ እኛ እየኖርንበት ነው። ለምን?
ዛሬ
Today
ከምንም ነገር በላይ እጅግ በጣም ውድ “ጊዜ” ሆኖ ሳለ፤ እኛ ግን ጊዜ ገዳይ ነን።ጫት የምንቀመው፤ ቁማር የምንቆምረው፤ሻይ ቤት ተቀምጠን ብዙ ሰዓታትን የምናሳልፈው፤ የስፔንና የእንግሊዝ ኳስ ጊዜአችንንም ሆነ ጭንቅላታችንን እንዲቆጣጠር የምንፈቅደው ለምን ቢባል የአብዘኛው ሰው መልስ ” ጊዜ ለመግደል” ። ወይም “ጊዜ ለማሳለፍ” የሚል ይሆናል።ጊዜ አላልፍ ብሎን ጊዜ ማሳለፊያ ምክንያት ፈላጊዎች ነን።ረቂቅ ሳይንስ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። በቀላሉ እድሜአችንን ለምን በከንቱ እናሳልፋለን?
ነገ
Tomorrow
ነገ የሚጸነሰው በዛሬ ውስጥ ነው። ዛሬ የነገ ወላጅ ነው። ስለዚህ ለዛሬ የሚደረገው መልካም ነገር ሁሉ፤ ጥሩ ነገ እንዲወለድ ያደርጋል።። በአጭሩ ነገ ዛሬ ይጀመራል። ስለዚህ ነገን መሥራት ከዛሬ ይጀምራል። ወደ አልጋችን ከመሄዳችን በፊት የሚስፈር፤የሚቆጠርና የሚመተር ሥራ መሥራታችንን ለራሳችን እርግጠኞች መሆን አለብን።