የኒኦ ሶሳይቲ አባልነት
1. መሥራች አባላትንና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ተቀባይነት ያገኙ አባላትን ይይዛል።
2. የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትውልድ-ኢትዮጵያዊና የውጪ ዜጋ ሆኖ የመኖሪያ ፍቃድ ያለው መደበኛ አባል መሆን ይችላል።
ሀ/ በኒኦ ሶሳይቲ ዓላማና ግብ የሚያምን፤ ለ/ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፤ ሐ/ የድርጅቱን የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በጠቅላላ ጉባዔ እና በሥራ አመራር በየጊዜው የሚወጡ የሥነ ምግባር ደንቦችን ተቀብሎ ተግባራዊ የሚያደርግ ፤
መ/ በጠቅላላ ጉባዔ በየጊዜው ስምምነት የሚደረግባቸውን ክፍያዎችን መክፈል የሚችል፤
ሠ/ በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ፤
3.አባልነትን በውርስ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ እንደማይቻል አውቆ የተረዳ፤
4. የኒኦ ሶሳይቲ አባል ወይም ሠራተኛ በመሆኑ ብቻ በድርጅቱ ንብረት ላይ ከአባልነት መብት ያለፈ መብት የሌለው መሆኑን የተስማማ፤
5.የአባላት መለዋወጥ በሶሳይቲው ሕልውና ላይ ተጽዕኖ እንደሌለው ዐውቆ የተረዳ፤
6.”የሶሳይቲው ገቢና ሀብት ለአባላት እንዲሁም ለሠራተኞች በሕግ ከተፈቀደ የአገልግሎት ክፍያ በቀር ሊከፋፈል አይችልም።” የሚለውን ሕግ የሚያከብር፤
የክብር አባላት
1 .የክብር አባላት ሶሳይቲው ውስጥ የመምረጥ፤ የመመረጥና ድምፅ የመስጠት መብት አይኖራቸውም፡፡
2.የኒኦ ሶሳይቲ አባል ያልሆኑና የኒኦ ሶሳይቲ ዓላማዎችን ለማስፈጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ፤ ሶሳይቲው በሚሰራባቸው ዘርፎች ተሰማርተው ውጤታማና የለውጥ አርአያ በመሆን በኒኦ ሶሳይቲ አባላት ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙ ግለ ሰቦች ወይም ድርጅቶች በሥራ አስፈጻሚ አቅራቢነትና በጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ የክብር አባል ይሆናሉ፡፡
4.የክብር አባላት በራስ ተነሳሽነት ካልሆነ በቀር የአባልነት መዋጮዎችንና ሌሎች ክፍያዎችን የመክፈል ግዴታ አይኖርባቸውም።.
የአባላት መብት
1.ሁሉም መደበኛ አባላት እኩል መብት አላቸው::
2.የኒኦ ሶሳይቲ አባልነት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው፡፡
3.ማንኛውም የኒኦ ሶሳይቲ መደበኛ አባል፡-
4. ለኒኦ ሶሳይቲ ዓላማዎችና ተልእኮዎች መሳካት የሚጠቅሙ ማናቸውንም አይነት ስራዎች ከሶሳይቲው ዓላማዎችና ተልዕኮዎች ክልልና መስመር ሳይወጡ የመስራት፣
5. የመምረጥ፣ የመመረጥና ስለ ሶሳይቲው እንቅስቃሴ ማንኛውንም መረጃ ጠይቆ የማግኘት፣
6. በጠቅላላ ጉባዔ የመገኘት፣ ስለድርጅቱ እንቅስቃሴ አዎንታዊ የሆነ ገንቢ አስተያየትና ድምጽ የመስጠት መብት አለው፡፡.
የአባላት መዋጮና ሌሎች ክፍያዎችን በሚመለከት
1.የኒኦ ሶሳይቲ መዋጮና ሌሎች ክፍያዎች የሚደረጉበት ጊዜና መጠን በጠቅላላ ጉባኤ ይወሰናል፡፡ አባላትም የሚከፍሉት መዋጮ ፤
2. አንድ መደበኛ አባል ነዋሪነቱ ከአፍሪካ ውጭ ከሆነ በዶላር፤ ኢትዮጵያ/አፍሪካ ውስጥ ከሆነ በብር ተመን የሚከፍሉ ይሆናል።
3.አንድ አባል በወር የሚከፍለው የአባልነት መዋጮ በጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰን ይሆናል።
4.ጠቅላላ ጉባዔው በሚወሰነው የጊዜ ገደብ የማይከፍል አባል ሥራ አስፈጻሚው በውሳኔ መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
5.የአባልነት መዋጮ ባለመክፈሉ ምክንያት በሥራ አስፈጻሚ የተጣለበትን ቅጣት ያልከፈለ አባል እዳውን እስኪከፍል ድረስ በጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምፅ አይሰጥም። ማንኛውንም የአባልነት መብቶችን መጠቀም አይችልም።
አባልነት ስለሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች
1.ማንኛውም/ዋም አባል የአባልነት መዋጮን በወቅቱ ለመክፈል ያለ ግዴታ ውዴታ የገባ፤
2.አንድ አባል ከአባልነት ከመሰናበቱ በፊት የሚፈለግበትን ዕዳ የመክፈል፣ በእጁ የሚገኘውን የሶሳይቲውን ንብረትና ሰነድ ከነይለፍ ቁጥሮች፤ፊደሎችና ምልክቶች ጭምር አረካካቢ አካል ባለበት የማስረከብ፤
3.ማንኛውም አባል የመተዳደሪያ ደንብ፣ በቦርድ የሚወጡ መመሪያዎችና ውሣኔዎችን የማክበር ፣
4.ማንኛውም አባል የኒኦ ሶሳይቲን አላማዎችና የገባቸውን ግዴታዎች የማክበር፣ የኒኦ ሶሳይቲውን ንብረት የመንከባከብና የሚጠበቅበትን አገልግሎት የመስጠት ፣
5.የኒኦ ሶሳይቲ መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት፤ መገኘት ካልቻለ በአብላጫ የተላለፉ ውሳኔዎችን የማክበርና የመፈጸም፤
6.ማንኛውም አባል ወንድም ሆነ ሴት ማህበሩ ከተቋቋመለት ዓላማዎች ውጭ አዲስ ዓላማዎችን :-
አንድ የኒኦ ሶሳይቲ አባል አባልነቱ የሚቋረጠው ፤
1.ሲሞት፣
2.መተዳደሪያ ደንቡ ላይ በተገለጸው መሠረት ወይም በሌላ አጥጋቢ ምክንያት ከአባልነት እንዲሰናበት ቦርዱ ሲወስን፣
3.የኒኦ ሶሳይቲ ክብርና ህልውና በሚነካ ወይም በሚያናጋ ተግባር ላይ መሳተፉ በማስረጃ ሲረጋገጥና ይህም ቦርዱ ሲወሰን፣
4.የኒኦ ሶሳይቲ ዓላማ መሳካት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተገቢውን ተሳትፎ ለማድረግ ፍቃደኛ ሳይሆን/ሳትሆን ስትቀር እና ይኸውም በቦርድ ሲወሰን፣
5.መዋጮውን ለአንድ አመት ያህል ጊዜ ባለመክፈሉ/ሏ በቦርዱ ከአባልነቱ/ቷ ሲሰናበት/ስትሰናበት፣
6.ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ችሎታው/ዋን ወይም መብቱን/ዋን ሲነጠቅ/ስትነጠቅ ወይም ከአባልነት ሲወገድ/ስትወገድ፣
7.የኒኦ ሶሳይቲ አባልነት በራሱ ፈቃድ ለመልቀቅ በጽሁፍ ሲጠይቅና በእጁ የሚገኙ የማህበሩን ንብረቶችና ስነዶችን አስረክቦ የስንብት ደብዳቤ ሲያገኝ ይሆናል።.
የኒኦ ሶሳይቲ አባላት ዓይነቶች
ሀ/ እጩ አባላት
ለ/ መደበኛ አባላት
ሐ/ የክብር አባላት
መ/ ተባባሪ አባላት
ሠ/ አጋር አባላት(በድርጅት ደረጃ).