ኒኦ ሶሳይቲ
NEO SOCIETY
አዲስ ማህበረሰብ ከዚህ ይጀምራል።

ዓለማችን ሕዝብ ከዛሬ አሥራ ሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ በታሪኩ ያሳለፋቸውን የማህበረሰብ ደረጃዎችን ማለትም የአዳኝነትና የፍራፍሬ ለቃሚነትን ፤ የከብት እርባታንና የእርሻን፤ የቅድመ -ዕደ- ጥበብንና ፤ የድህረ- ኢንደስትሪን ዘመን አልፎ በኢንፎርሜሽን ሶሳይቲ ውስጥ ይገኛል። እኛም የዓለም ሕዝብ አካል እንደመሆናችን መጠን የተወሰነ ደረጃ ብንራመድም ፤ በዓለም ሕዝብ ፊት አንገት የሚያስደፋን ነገር አለ ። ይኼውም ከዛሬ አሥራ ሁለት ሺህ ዓመት በፊት የማህበረሰብ ደረጃ ነበር የሚባለውን የድንጋይ ዘመን ፤ እኛ በዚያ ዘመን ውስጥ ዛሬም እየኖርን መሆናችን ነው። ማናቸውንም የዕድገት ደረጃዎችን አለመጨረሳችን አሳፋሪ ገጽታችን ነው። ለምን ?


ራእይ
VISION

እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ2040 ዓ.ም ለአእላፋት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥራና የእንጀራ ምንጭ መሆን፤

በ2040 ዓ.ም አእላፋት የኢትዮጵያ ሕዝብ ማለት?

የተባበሩት መንግስታት የስነ-ሕዝብ ጥናት ፕሮጄክት፦ ከዓለማችን አገሮች መካከል ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት የሚያሳዩ ናቸው ከተባሉት ስምንት አገሮች ሕንድ፤ ናይጄሪያ፤ፓክስታን፤ዴሞክረቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ ታንዛኒያ፤ፊሊፒንስ ፤ ግብጽ እና ኢትዮጵያ  ናቸው። ኢትዮጵያ በዚህ ፕሮጄክት ስሌትና ተምኔት መሠረት፤ በ1850 ዓ.ም 18 ሚሊዮን 434 ሺህ ሕዝብ፤ በ1900 ዓ.ም 18 ሚሊዮን 434 ሺህ ሕዝብ  (በ50 ዓመታት ውስጥ ለውጥ አላሳየም።)  በ1950 ዓ.ም 18 ሚሊዮን 128 ሺህ (ቅናሽ አሳይቷል።)  በ2000ዓ.ም  66 ሚሊዮን 225ሺህ ሕዝብ( ከፍተኛ እድገት ነው።)  በ2050 ዓ.ም 213 ሚሊዮን 190ሺህ ሕዝብ ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል። ይህ ማለት ከኒኦ ሶሳይቲ ራእይ ፍጻሜ 2040 ዓ.ም አንድና ሁለት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው። በ2100 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ 323 ሚሊዮን 283ሺህ ሕዝብ እንደሚያድግ የተባበሩት መንግስታት ስነ-ሕዝብ ፕሮጄክት ያሳያል። በዚሁ በ2100 ዓ.ም የአሜሪካ ሕዝብ 393 ሚሊዮን 993ሺህ እንደሚደርስ ግምት አለ። ማነጻጸር ይቻላል።

.

ኢትዮጵያ በ2050 ዓ.ም
ከምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ጋራ ስትወዳደር

ኤሪትሪያ 5ሚሊዮን 925ሺህ ሕዝብ፤

ጂቡቲ 1ሚሊዮን 498ሺህ ሕዝብ፤

ሶማሊያ 36ሚሊዮን 089ሺህ ሕዝብ፤

ኬንያ 84ሚሊዮን 724 ሺህ ሕዝብ፤

ደቡብ ሱዳን 17ሚሊዮን353ሺህ ሕዝብ፤

ሱዳን 83 ሚሊዮን 779 ሺህ ሕዝብ……

ይደርሳሉ ተብለው ሲገመቱ…ኢትዮጵያ 213ሚሊዮን 190ሺህ ሕዝብ እንሆናለን ማለት ነው። ለመቀበል የሚያስቸግር የሕዝብ ዕድገት ይጠብቀናል። ይህን እጥፍ የሕዝብ ዕድገትን የሚቋቋም ሶሺዮ-ኢኮኖሚ ካልተፈጠረ የመጪው ትውልድ ዕጣ-ፈንታ አስጨናቂ ነው። በአጠቃላይ የዓለም ሕዝብ ብዛት በ2050 ዓ.ም 9.7ቢሊዮን ሲሆን፤ በ2100 ዓ.ም 10.4 ቢሊዮን ሕዝብ ብዛት ይሆናል ተብሎ ተገምቷል።


ኒኦ ሶሳይቲ በዚህ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ግሽበት ከፈጠረው ጭንቀት ውስጥ ቆሞ የሥራና የእንጀራ ምንጭ የመሆን ራእይ አይቷል። እንዴት ይሆናል? ቀላል ጥያቄ ከባድ መልስ ይፈልጋል። የሕዝብ ብዛት ቁጥርን በቤተሰብ ደረጃ መመጠን፤ የማህበረሰቡን ኑሮ ማሻሻል፤ ለራእይነት ተነሳሽነትን መፍጠር፤ አዎንታዊነትን ማጎልበት፤ የሕዝብ ምርጫ ዕድሎችን ማስፋት የሁሉንም ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የመንግስት፤ የሲቪክ ድርጅቶች ፤የሐይማኖት ተቋማት፤ የግሉ ዘርፍ እና የዳያስፖራ ማህበረሰብ ጽኑ ድጋፍና ቀና ትብብር እንዲሁም የሰፊው ሕዝብ ተሳትፎ በእጅጉ ያስፈልጋል። ይህ ፍላጎትና ፈቃድ ብቻ ሳይሆን ለሕልውና ዘለቄታ ሲባል ግዴታም ጭምር ነው።  ስለሆነም ኒኦ ሶሳይቲ በ2040 ዓ.ም 50ሚሊዮን ለሚጠጋ ሕዝብ የሥራና የእንጀራ ምንጭ ለመሆን ራእይ አይቶ፤ ግብ ተክሎ፤ ዓላማ ይዞ ሜጋ ፕሮጄክቶችን አቅዶ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል። በአከባቢ፤ በማህበራዊ፤ በባህላዊ፤ በኢኮኖሚያዊ፤ በቱሪዝምና በአገልግሎት ዘርፎች ሲሰማራ ከሁለት መቶ በላይ ድርጅቶችን ያቋቁማል። ማለትም ሆስፒታሎችን፤ ትምህርት ቤቶችን፤ ገበያ ማዕከሎችን፤ ፓርኮችን፤ ሆቴሎችን፤ ግብርናን፤ ንግድና ኢንዱስትሪን፤ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤንና ሌሎች አያሌ የሥራ ዘርፎችን በመክፈትና በማስፋፋት የሥራ ዕድልና የእንጀራ ምንጭ ለመሆን ይሠራል።


ስለኒኦ ሶሳይቲ
ከተሰጡት ንግግሮች መካከል

በኒኦ ሶሳይቲ ምሥረታ ቀንና በአንደኛ ዓመቱ ክብረ- በአል ላይ
ከተደረጉ ንግግሮች የተቀነጨቡ….

ማግኔት እውነተኛ ብረቶችን ይስባል።

ኒኦ ሶሳይቲ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ማግኔት ሆኖ ያሰባስባል ብዬ አምናለሁ።”

ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷአለም
የኢፌዴሪ ሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር


የአገር ቤቱን ሕዝብና ዳያስፖራውን በአንድ ዐውድ አሰባስቦ ወደ ተግባራዊ የልማት እንቅስቃሴ ለመግባት የተነሳ አዲስና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ነው። .”

ዶር መሀመድ እንድሪስ
የዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

. 

ኒኦ ሶሳይቲ ሃሳቡ ሲጠነሰስ ጀምሮ አውቀዋለሁ። ዛሬ እውን ሆኖ ሥራ ላይ ነው ።ፈተናዎች እንደሚበዙ እገምታለሁ። ይሁን አንጂ መቶ ሺህ አባላት የማደራጀት ግቡንም እንደሚያሳካ አልጠራጠርም ።”

ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ
የኢፌዴሪ ሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲ’ ኤታ


ተልእኮ
MISSION

ከ21ኛ ክፍለ ዘመን ጋራ የሚራመዱ ሰዎችን በማሰባሰብና በማህበረሰብ ማዕቀፍ በማደራጀት፤ በተለያዩ የሙያ፤የሥራና የጥናት ዘርፎች ላይ በተግባር እንዲሰማሩ በማብቃት የድርሻቸውን አገራዊ አስተዋጽኦ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲያደርሱ የማስቻል፤

.

መርህ ቃል
MOTTO

አእላፍ ደጀን ከሠራ በጋራ፤

እንኳን ሰው ሠራሽ ሤራና መከራ፤

ይፈርሳል የተፈጥሮ ተራራ።


የ ኒ ኦ ሶ ሳ ይ ቲ ም ሥ ረ ታ

ጳጉሜን 01/2022 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተመሠረተ።